በሠ.ማ.ጉ. ሚ/ር ፣ አይ ኤል ኦ እና ፣ ቢ ኤም ዜድ ትብብር ለኮቪድ ምላሽ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሠራተኞች የስራ ዋስትና መርሀግብር

FDRE
MOLSA
POESSA
CEEF
CETU
IFT
ILO
BMZ

የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሠራተኞችን መጠበቅ ፡ የሙያ ጤንነትና ደህንነት እና የገቢ ድጋፍ ለኮቪድ 19 ተላላፊ በሽታ ምላሽ

 የሠ.ማ.ጉ. ሚ/ር፣ አይ.ኤል.ኦ. እና ቢ.ኤም ዜድ የሥራ ዋስትና መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ለተከሰተው የኮቪድ 19 ቀውስ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር የሚሰጥ ድንገተኛ ድጋፍ አካል ሲሆን የገንዘብ ድጋፉን ያበረከተው የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር (ቢኤምዜድ) ነው፡፡ መረሀ ግብሩ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ድርጅት (የግ.ድ.ሠ.ማ.ዋ.ኤ) ተመዝግበው  በሚገኙ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችን ደመወዝ ወጪ በመሸፈን ፋብሪካዎቹ ሠራተኞቹን በሥራ ላይ እንዲያቆዩ ለማበረታታት ነው፡፡

ይህ መርሀ ግብር በዓለም አቀፍ የማህበራዊ ዋስትና ደረጃዎች ከተቀመጡ መርሆዎች ጋር የተዛመደ ሲሆን፣ መብትን መሠረት ያደረገ የማህበራዊ ጥበቃ፣ ማህበራዊ ምክክር፣በገንዘብ የመደጋገፍና ዘላቂነት አሰራርን ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፖሊሲዎች ጋር እንዲጣጣም ተደርጐ የሚተገበር ነው፣

ይህ መርሀ ግብር የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር ሠራተኞች በኮቪድ 19 አማካኝነት የሚመጣባቸውን ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ተጋላጭነት ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፣ በተለይም ፋብሪካዎቹ የሰው ኃይላቸውን በሥራ ላይ እንዲያቆዩ በማድረግ በቀጣይም ዘለቄታነት እና ችግርን የሚቋቋም የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ነው፡፡ 

የሚሰጡ ጥቅሞች

የሚሰጡ ጥቅሞች ተብሎ የተመለከተው ለመረሀግብሩ ብቁ ለሚሆኑ ፋብሪካዎች ሠራተኞች ወርሀዊ ደመወዝን መክፈል ነው፡፡ ይህም የሚሰላው በመረሀግብሩ የጊዜ ሽፋን በፋብሪካው ተቀጥረው የሚገኙ ሠራተኞች ቁጥር ከሙሉ ደመወዛቸው ጋር ተባዝቶ የሚገኘው መጠን ነው፡፡ መረሀ ግብሩ የሚከፍለው ሙሉ ደመወዝን[1] ነው፡፡ 

 • ሠራተኞች የሚለው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ላይ የተመለከተውን ትርጉም የሚወስድ ሲሆን የማኔጅመንት አባላትን አይጨምርም፡፡
 • ለዚህ መርሀ ግብር ለኢትዮጵያ የተዘጋጀው በጀት በአሜሪካ ዶላር 4.5 ሚሊየን ሲሆን፣ ይህም (181,631,779.1 ብር) የሚጠጋ ነው፡፡ 
 • [1] ሙሉ ደመወዝ ማለት የሠራተኛውን ዋነኛ ደመወዝ የሚመለከት ሆኖ የትርፍ ስራን፣የትራንስፖርት፣የቤት ኪራይ አበልንና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን አይጨምርም፡፡ 

የሚከተለው ክፍል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር ፋብሪካዎችን ብቁነት ለመመዘን የተቀመጠው ባለ ሁለት ደረጃ ምዘና ነው፡፡

ደረጃ 1  የምዝገባ ቅፅ

ለመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ መሆን የሚሹና ብቁ የሚሆኑ ፋብሪካዎች የሚከተለውን የምዝገባ ቅፅ በመጠቀም ማመልከቻ በማስገባት መመዝገብ ይችላሉ፡፡ 

 ማሳሰቢያ:- ለዚህ መርሀ  ግብር ተጠቃሚነት ሠራተኞች ብቁ ከሆኑ ፋብሪካዎች በግል ማመልከት አይገባቸውም፡፡

ደረጃ 2 የብቁነት መጠይቅና ተፈላጊ ማስረጃዎች ስለማቅረብ

ለዚህ የሥራ ዋስትና ድጋፍ የሚደረግ ምዝገባን ለማከናወን አመልካች ፋብሪካዎች የምዝገባ ቅጹን በሞሉ በሁለት ሳምንት ውስጥ በድህረ-ገጽ ውስጥ በኢሜል አድራሻቸውና የይለፍ ቃል ተጠቅመው ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ የሚያደርግ መልእክት እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡

 በድህረ-ገጽ መግባት እንደቻሉ አመልካቾች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በድህረ-ገጽ ላይ በማስቀመጥ ማመልከቻቸውን ማጠናቀቅ ይገባቸዋል፡፡ 

ለዚህ ተግባር የተቋቋመው የሦስትዮሽ ኮሚቴ ማመልከቻዎች በተጠናቀቁ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ማጣራት  በማድረግ አመልካች ፋብሪካዎች ድጋፉን ለማግኘት ብቁ ስለመሆናቸው ወይም ስላለመሆናቸው ያሳውቃል፡፡ 

 ሁሉም አመልካቾች ለመረሀ ግብሩ ብቁ ስለመሆናቸው ወይም ስላለመሆናቸው የተወሰነው ውሳኔ እንዲደርሳቸው ተደርጎ ብቁ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው ፋብሪካዎች ዝርዝር በድህረ-ገጽ ላይ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ያልተሟሉ ማመልከቻዎች በቀጥታ የሚሰረዙ ይሆናሉ፡፡

ለሥራ ዋስትና መረሀግብሩ የብቁነት መመዘኛ

ለሥራ ዋስትና መርሀግብር ብቁ ለመሆን ፋብሪካዎች የሚከተሉትን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡ 

 • በኢትዮጵያ ውስጥ በንግድ ስራ ለመሰማራት ፈቃድ ያላቸው፣
 • በግል ድርጅቶች ማህበራ ዋስትና የተመዘገቡና የ2012 በጀት ዓመት መዋጮዎችን የከፈሉ
 • ማንኛውንም ተመሳሳይ የደመወዝ ድጎማ ከሌሎች የልማት አጋሮች፣ ከመንግሥት ወይም ከግል ተቋማት ተጠቃሚ ያልሆኑ ፋብሪካዎች፣
 • በ2012 በጀት ዓመት የኤክስፖርት ወይም የሽያጭ ወይም የሥራ ትዕዛዝ መቀነስ ወይም የትርፍ ገቢያቸው ስለመቀነሱ የኦዲት የሂሳብ ሰነድ ከሕጋዊ የኦዲት ተቋም ማቅረብ የሚችሉ

   የሚያስፈልጉ ሰነዶች ማረጋገጫ ዝርዝር

     • የሁለት ዓመት ማለትም ከግንቦት 2010 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለው የሽያጭ መረጃ እንዲሁም የትርፍና የኪሳራ ማረጋገጫ፣
     • ድጋፍ ለሚደረግበት ጊዜና ከድጋፍ በኋላ ለ3 ወራት በሥራ ላይ ሠራተኞቻቸውን ማቆየት የሚችሉ ፋብሪካዎች፣
     • የድጋፍ ማመልከቻ ካስገቡበት ጊዜ ጀምሮ ለቀጣይ ስድስት ወራት በቂ የሥራ ካፒታል ስለመኖሩ ማረጋገጫ ያላቸውና የምርት ትንበያ/ዕቅድ ማቅረብ የሚችሉ፣
     • በ2011፣ በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የነበሩትንና ያሉትን ሠራተኞች ዝርዝር (ሙሉ ስም፤የትውልድ ቀን፣ ፆታ፣አድራሻ፣ሃላፊነት ያከተተ) ማቅረብ የሚችሉ፣
     • ለሠራተኞቻቸው የጥር ወር 2011 ዓ.ም እና ከነሐሴ 2012 እስከ ጥር 2013 ዓ.ም. ድረስ ወርሃዊ ደመወዝ የከፈሉበትን መዛግብት ማቅረብ የሚችሉ፣
     • የ2012 በጀት ዓመት የገቢ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ፣
     • በ2012 በጀት ዓመት የጡረታ መዋጮ የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
     • የደመወዝ ድጋፍን ካገኙ ከ3 ወር በኋላ ከንግድ ሥራዉ ለማገገም ስለመቻላቸውና ሥራውን ስለመቀጠላቸው እንዲሁም ስለቀጣይ ዕቅዳቸው ዝርዝር ማብራሪያ ማለትም፡-
     • ፋብሪካው የሰው ኃብቱን ለማልማት የወሰዳቸው የተለያዩ ጥረቶች
     • ኮቪድ 19 የመሳሰሉ ወረርሸኞች በሚያጋጥሙበት ወቅት በፋብሪካው የጤና አጠባበቅና የስራ ቦታ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚከናወን የመረጃ ስርዓት

     የሚከተሉት ፋብሪካዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡-

     • በኢትዮጵያ የፀደቁ የዓለም ሥራ ድርጅት መሠረታዊ ስምምነቶች (የሠራተኛ ማህበር መኖር፣ የተመዘገበ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ኮሚቴ፣ የህብረት ስምምነት ሰነድ፣ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ የሚችሉ)
     • ለዓለም ሥራ ድርጅት የተሻለ ሥራ መርሀ ግብር የተመዘገቡ
     • የሁለትዮሽ የማህበራዊ ምክክር በፋብሪካው ስለመተግበሩ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል

     ይህ መርሀ ግብር እንደ አስፈላጊነቱ የመረሀግብሩ ተጠቃሚዎችን በሦስተኛ ወገን ኦዲት የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

     የሁለት ዓመት ማለትም ከግንቦት 2010 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለው የኤክስፖርት እና የሽያጭ መረጃ እንዲሁም የትርፍና የኪሳራ ማረጋገጫ፣

   የምልመላ ሂደቱ ምንድነው ?  

   1. የምዝገባ ቅፅ መሙላት
   2. የብቁነት መጠይቅን ለማግኘት የሚየስችል ‹‹ማገናኛ›› (Link) መቀበል
   3. ወደ መጠይቁ ገፅ በመግባት የማመልከቻውን ቅፅ በአመልካች ፋብሪካው መሙላት
   4. በአመልካች ፋብሪካ ተያያዥነት ያለቸውን ሰነዶችን በድህረ ገጽ ላይ መጫን
   5. ማመልከቻውን መቀበልና በሦስትዮሽ የቴክኒክ ኮሚቴ ማጣራት
   6. የብቁነት ወይም ብቁ አለመሆን በአብይ ኮሚቴ ተረጋግጦ በኢሜል ለአመልካቾች እንዲላክ ማድረግ
   7. ለፋብሪካ ሠራተኞች በባንክ በኩል ደመወዛቸውን ማስተላለፍ

   ጥቅሞቹ ምንድን ናቸው ?.

   አንድ ፋብሪካ የተመለከተውን የብቁነት መመዘኛ መስፈርት ሲያሟላ በወርሃዊ የደመወዝ መክፈያ ፔሮል ላይ ላሉ ሠራተኞች (የማኔጅመንት አካላትን ሳይጨምር) የወር ክፍያ ያገኛል፣

   • ፋብሪካዎች የሠራተኞቻቸውን ጥቅል ሙሉ ወርሃዊ ደመወዝ እንዲከፈሉ ይደረጋል
   • ተጠቃሚ የፋብሪካ ሠራተኞች የድጋፍ ደመወዛቸውን በባንክ በኩል በቀጥታ የሚተላለፍላቸው ይሆናል፡፡ ለባንክ የሚከፈል የማስተላለፊያ ክፍያ በመርሀ ግብሩ የሚሸፈን ይሆናል
   • ከ45 ቀን በላይ ኮንትራት ላላቸው ሠራተኞች መርሀ ግብሩ ከሠራተኛው ጥቅል ደመወዝ መከፈል ያለበትን የ7 በመቶ የጡረታ መዋጮ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በመክፈል ሠራተኞች በዋስትና አቅድ ውስጥ ተሸፍነው እንዲቆዩ ያደርጋል
   • ከፍተኛው የድጋፍ ጊዜ ሦስት ወር ሲሆን ይህም በበጀት መኖር ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡

    ማሳሳቢያ፡ በአሠሪው ይከፈል የነበረው 11 በመቶ የሠራተኞች የጡረታ መዋጮ በፋብሪካው የሚሸፈን ሆኖ ይህም ለመርሃ ግብሩ አፈፃፀም ፋብሪካው በቅድመ ሁኔታነት የሚከፍለው ይሆናል፡፡

    ግብረ መልስ መስጠትና ቅሬታን ስለማቅረብ?

    በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች ጥያቄ 7ትን ይመልከቱ ወይም መልእክት በኮንትራት ቅፁ አማካኝነት ያቅረቡ

    አስቀድመው ተመዝግበዋል?

    የብቁነት መመዘኛው ደርጅትዎን የሚመለከት ከሆነ ከዚህ በታች ያለውን ቁልፍ በመጫን ይመዝገቡ፡፡