ጥያቄ 1፡ የኢትዮጵያ የሥራ ዋስትና መርሀ ግብር ምንድነው?

ይህ መርሀ ግብር የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር ሠራተኞች በኮቪድ 19 አማካኝነት የሚመጣባቸውን ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ተጋላጭነት ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፣ በተለይም ፋብሪካዎቹ የሰው ኃይላቸውን በሥራ ላይ እንዲያቆዩ በማድረግ በቀጣይም ዘለቄታነት እና ችግርን የሚቋቋም የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ነው፡፡ 

የሥራ ዋስትና መርሀ ግብሩ አውድና ዋና መገለጫዎች

 የሠ.ማ.ጉ.ሚ/ር፣ የአይ.ኤል.ኦ. እና ቢ.ኤም ዜድ የሥራ ዋስትና መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ለተከሰተው የኮቪድ 19 ቀውስ ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር የሚሰጥ ድንገተኛ ድጋፍ አካል ሲሆን የገንዘብ ድጋፉን ያበረከተው የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር  (ቢኤምዜድ) ነው፣ 

መርሀ ግብር

ይህ መርሀ ግብር በዓለም አቀፍ የማህበራዊ ዋስትና ደረጃዎች ከተቀመጡ መርሆዎች ጋር የተዛመደ ሲሆን፣ መብትን መሠረት ያደረገ የማህበራዊ ጥበቃ፣ ማህበራዊ ምክክር፣በገንዘብ የመደጋገፍ፣ ዘላቂነት እና አሰራሩም ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የሥራ ስምሪት ፖሊሲዎች ጋር እንዲጣጣም ተደርጐ የሚተገበር ነው፡፡

 ይህ መርሀ ግብር የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሴክተር ሠራተኞች በኮቪድ 19 አማካኝነት ከሚፈጠር ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎችና ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፣ በተለይም ፋብሪካዎቹ የሰው ኃይላቸውን በሥራ ላይ እንዲያቆዩ በማድረግ በሂደትም ዘላቂና ችግርን የሚቋቋም የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ነው፡፡ 

ይህ መርሀ ግብር ኢትዮጵያን ጨምሮ በተመረጡ ሀገራት በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተሰማሩ አካላትን ለመደገፍ በመንግስትና በግል ሴክተር ትብብር በዓለም ሥራ ድርጅት የተቀረፀ ሲሆን ይህም፡-

 (i) የሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ እርምጃዎችን በማጠናከር አሰሪዎች፣ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከሚመጡ የኮቪድ 19 የጤና ስጋቶች እንዲጠበቁ እና           መሰል ድንገተኛ በሽታዎች መከሰት ከደካማ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራ አመራርና አደጋዎች ጋር ተያይዞ የሥራ ቦታዎችን ለአሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያጋልጥ ለማድረግ፣

(ii) ድርጅቶች ለሚያጋጥማቸው የሥራ ስምሪት እና የገቢ ማጣት ድጋፍ ለማድረግ እና ሠራተኞች በኮቪድ 19 ምክንያት ለገቢ እጦት እንዳይጋለጡ የደመወዝና ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በመስጠት ማካካስ እና የሥራ ግንኙነቶች ወደ ቀድሞ መደበኛ ሁኔታዎች ተመልሰው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ነው፡፡  

 የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የመርሀ ግብሩን የገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈፅም ይሆናል፡፡ ለዚህ ሥራ የሚ/ር መ/ቤቱ ከግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ይህ መርሀ ግብር በጀርመን መንግሥት አነሳሽነት የተጀመረ (በፌዴራል የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚ/ር (BMZ) እና በፌዴራል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር (BMA) በመወከል) የቪዥን ዜሮ ፈንድ ማርች 27/2020 የአብይ ኮሚቴ በአካሄደው ስብሰባ ላይ በተደረሰው ስምምነት መሠረት የመጀመሪያ ዙር በቢ.ኤም.ዜድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲከናወን የታሰበ መርሀ ግብር ነው፡፡ ይህ መርሀ ግብር እንደባለብዙ ግብረ-ሰናይ መርሀ ግብር ሌሎች የልማት አጋሮች እንዲሳተፉበትና መርሀ ግብሩን  እንዲያሳድጉት ዓልሞ ተቀረፀ ነው፡፡

ይህ መርሀ ግብር ደግሞ ከኮቪድ 19 ጋር የተያየዙ ሥራዎችን ለማስፈጸም የሚያግዝ ሲሆን፣የዓለም አቀፍ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪን በተለይም የጨርቃ ጨርቅ ሠራተኞችን ገቢ፣ ጤናና የሥራ ዋስትና ለመጠበቅ፤ እንዲሁም በኮቪድ 19 ቀወስ ወቅት አሠሪዎች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለመደገፍ እና ዘላቂ የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓት በመዘርጋት የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ የተሻለና ችግሮች መቋቋም እንዲችል በጋራ ለመስራት ነው፡፡ 

ጥያቄ 2: ማን ማመልከት ይችላል?
 • ለዚህ ድጐማ መርሀ ግብር ብቁ መሆንዎን ያረጋግጡ

  ለዚህ መርሀ ግብር ብቁ የሚሆኑት ማንኛቸውም ሃገር በቀል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ሥራ ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎችና ከዚህ የሚከተለውን የመመዘኛ መስፈርቶች ያሟላ ይሆናሉ፡-

 • ከሌሎች የልማት አጋሮች፣ ከመንግሥት ወይም ከግል ድርጅቶች የደመወዝ ድጐማ ድጋፍ ተጠቃሚ ያልሆኑ፣
 • ለማህበራዊ ዋስትና መዋጮ እየከፈሉ ያሉ ፋብሪካዎች ፣
 • ለሠራተኞቻቸው ወርሃዊ ደመወዝ ለመክፈል የተቸገሩ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፋብሪካዎች (በጥያቄ 4 ላይ የተመለከተውን ማስረጃ)፣
 • በመረሀ ግብሩ ለተመለከተው ጊዜ ሠራተኞቻቸውን ሙሉ ደመወዝ እየከፈሉ ማሠራት የሚችሉ፣
 • በመርሀ ግብሩ የተቀመጡ አቅጣጫዎችንና ለሥራ ዋስትና ድጋፍ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አክብረው ለመተግበር ፈቃደኛ የሆኑ፣
 • በሀገሪቱ አገር አቀፍ የሥራ እጥነት ዋስትና የድጋፍ ሥርዓት እንዲሰፍን በሚደረግ ውይይት ላይ በንቃት ለመሳተፍ ቁርጠኛ የሆኑ ፡፡
 •  

   

  ከዚህ በታች ያሉትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ ፋብሪካዎች  ተጠቃሚነታቸው ወይም ተመራጭነታቸው ከፍ ያለ ሲሆን ሁኔታዎቹም፡-

  • አገሪቱ ያፀደቀቻቸውን የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት መሠረታዊ ስምምነቶችን በቁርጠኝነት በሥራ ላይ ያዋሉ ፋብሪካዎች፣
  • ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተጋላጭ ሠራተኞችን የያዙ ፋብሪካዎች፣
  • በዓለም የሥራ ድርጅት የተሻለ የሥራ መርሀ ግብር ውስጥ የተመዘገቡ ፋብሪካዎች፣
  • በሥራ ቦታ የሥራ ደህንነት ኮሚቴ ሥርዓት የዘርጉ ፋብሪካዎች፣
  • በሥራ ቦታ የሁለትዮሽ ማህበራዊ ምክክር በመተግበር ላይ የሚገኙ፣
  • ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ዕውን ለማድረግ አግባብነት ያለውን መረጃ ከሠራተኞቻቸው ጋር ለመለዋወጥ የአሠራር ሥርዓት ዘርግተው የተገበሩ፣

   

  ጥያቄ 3 ፡ መቼ ማመልከት ይችላሉ?

  የማመልከቻ የመጨረሻ ጊዜ ::

   ከላይ የተመለከተውን መመዘኛ የሚያሟሉ ፋብሪካዎች በሠ.ማ.ጉ.ሚ/ር በሚወጣው ማስታወቂያ ከተመለከተው የመጨረሻ ቀን በፊት ማመልከት ይገባቸዋል፡፡

   ማመልከቻ ለማስገባት ከተመለከተው ቀን በፊት ተሟልቶ በበይነ መረቡ የቀረቡ ማመልከቻዎች ብቻ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡

   ለዝርዝር የማመልከቻ አቀራረብ ጥያቄዎች በተራ ቁጥር 5 እንዴት ማመልከት ይቻላል የሚለውን ወይም በ (contact@saving-jobs.org) ይጠቀሙ፡፡

  ጥያቄ 4 : የትኞቹ ሠራተኞች ብቁ ናቸው ?

  የትኞቹን ሠራተኞች በድጋፍ በመረሀ ግብሩ ውስጥ ማካተት ይችላሉ?

   ፋብሪካው በቴክኒክ ኮሚቴ በሚያዘጋጀው ተጠቃሚዎች ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ እና የመርሃ ግብሩ አብይ ኮሚቴ ሲያጸድቅ (በተ.ቁ. 5 ለዝርዝር ጉዳይ እንዴት ማመልከት ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ) ከማኔጅመንትና የአስተዳደር አካላት ውጭ በፋብሪካው ውስጥ በደመወዝ መክፈያ ፔሮል ላይ የተዘረዘሩ ሰራተኞችና  በማመልከቻው ውስጥ የተጠቀሱ ሠራተኞች የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ ሆነው ሊካተቱ ይችላሉ፡፡

  ጥያቄ 5: እንዴት ማመልከት ይቻላል?

  ለደመወዝ ዋስትና መርሀ ግብር እንዴት ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል?

  • የሠ.ማ.ጉ.ሚ/ር የመርሀ ግብሩን ሥራ መጀመር በሕዝብ መገናኛ ብዙሀን፣ በማህበራዊ ሚዲያ እንዲሁም saving-jobs.org በሚለው ድህረ-ገጽ ላይ ማስታወቂያ ያወጣል፣
  • የምዝገባ ቅፁን በመሙላት ወደሚቀጥለው የብቁነት መጠየቅ መግቢያ መረብ የሚገቡበት ቁልፍ “ማገናኛ” ያገኛሉ፣
  • የብቁነት መጠይቁን በማገናኛው ተደግፈው በመሙላት እና አስፈላጊ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ ወይም መጫን፡፡ የተሟላ ማመልከቻ ብቻ ለምዘና የሚቀርብ ይሆናል፡፡
   ጥያቄ 6፡ ካመለከቱ በኋላ

   የተመለከተው የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ የሠ.ማ.ጉ.ሚ/ር፡-

   • የፋብሪካዎችን ማመልከቻ ያጣራል/ይመረምራል፣
   • በፋብሪካዎች የቀረቡ ማስረጃዎችንና ማመልከቻዎችን በመመርመር እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ መረጃ ይጠይቃል፣
   • አመልካች ፋብሪካዎች ከሌሎች የድጋፍ መረሀ ግብሮች ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ያረጋግጣል፣
   • በሠ.ማ.ጉሚ/ር የሚመራና የአሠሪዎችና የሠራተኛ ማህበራት፣ የሚኒስቴር መ/ቤት እና የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካዮች የሚገኙበት ገለልተኛ የቴክኒክ ኮሚቴ በፋብሪካዎች የቀረቡትን የሂሳብ ሰነዶች ያጣራል፣
   • የሠ.ማ.ጉሚ/ር ማመልከቻዎችን በመምርመርና በማጣራት በተቀመጠው መመዘኛ መስፈርት መሠረት ብቁ የሆኑ ፋብሪካዎችን በመለየት ዝርዝራቸውን ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለአብይ ኮሚቴው ያቀርባል፡፡

    የሦስትዮሽ አብይ ኮሚቴው፡-

    • ከማስረጃዎች ጋር ተያይዞ የቀረበለትን የፋብሪካዎችን የውሳኔ ሃሰብ ዝርዝር በመመርመር የመጨረሻ የተጠቃሚ ድርጅቶችን ዝርዝር ያጸድቃል፣
    • ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ካላገኘ የሠ.ማ.ጉ ሚ/ር ማመልከቻው ተቀባይነት ያላገኘበትን ምክንያት በማመልከት በኢሜል ያሳውቃል፡፡ በውሣኔው ላይ ቅሬታ ካለ ውሣኔው በደረሰ በሁለት ሳምንት ውስጥ አቤቱታ ለሠ.ማ.ጉሚ/ር ማቅረብ ይቻላል፡፡

     

    የቅሬታ አቀራረብ ሂደት:-

    • ፋብሪካዎች አቤቱታቸውን በዚህ በድህረ-ገጽ ላይ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ይሞላሉ፣
    • የሚቀርቡ አቤቱታዎች በቴክኒክ ኮሚቴዉ በየሁለት ሳምንቱ ይመረምራሉ፣
    • የቴክኒክ ኮሚቴው የቀረቡ አቤቱታዎችንና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማካተት ለአብይ ኮሚቴ በማቅረብ ውሣኔ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ አብይ ኮሚቴው በቴክኒክ ኮሚቴው መፍትሄ ያላገኙ ጉዳዮችን በመመርመር ውሣኔ ይሰጣል፣
    • ፋብሪካዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለአቤቱታዎቻቸው ምላሽ እንዲያገኙ ይደረጋል፣
    • ያልተሟሉ ማመልከቻዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    •  ተጠቃሚ ፋብሪካዎች:-

     • ድርጅቱ የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ እንዲሆን የተመረጠ መሆኑን ለሠራተኞች ማህበር ወይም በቀጥታ ለሠራተኞቹ ማሳወቅ ይኖርበታል፣
     • መርሀ ግብሩ እንደአስፈላጊነቱ የተጠቃሚ ፋብሪካዎችን የድጋፍ አሰራር በሦስተኛ ወገን ኦዲት የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
     • የተጠቃሚ ፋብሪካ ሠራተኞች ሙሉ ወርሃዊ የደመወዝ ክፍያቸው በባንክ በኩል ይፈፀማል፡፡ የባንክ ማስተላለፊያ ወጪዎችም በመርሀ ግብሩ የሚሸፈን ይሆናል፡
    ጥያቄ 7፡ ስለ መርሐ ግብሩ ለማወቅ እንዴት ሊያገኙን ይችላሉ?

    አጠቃላይ ስለመርሀ ግብሩ ለሚኖሮት ጥያቄ እባክዎ ‹‹አድራሻ›› የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ

    (ማስታወሻ፡አድራሻ የሚለውን ማገናኛ መጠቀም ወደሚመለከተው ያግኙን ወደሚለው ገፅ እንዲያመሩ የሚያግዝ ነው)

     በመርሀ ግብሩ ስለሚካተቱ ተጠቃሚ ፋብሪካዎች ዝርዝር ውሳኔ ከታወቀ በኋላ አቤቱታ ወይም ቅሬታ ለማቅረብ ከዚህ በታች በተመለከው ቁልፍ በመጠቀም ማቅረብ ይቻላል፡፡